Embassy of Ethiopia
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊንና ትውልዯ ኢትዮጵያዊያን አስቀድመን የከበረ ሠላምታችንን እያቀረብን፡
በስዊዲን የምትገኙ ሁላችሁም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በስዊድን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመነጋገር መልካም እሳቤን ይዘን ወደ እናንተ መተናል፡፡ ይሔውም ሁለንም ኢትዮጵያውያን ያሳተፈና ያካተተ ጠንካራና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ተደራሽ የሚሆን ማህበረሰብን (ኮሚኒቲ) መፍጠር ነው፡፡
ይህ መልካም ጅማሮ በጤንነት ባለው ቦታ ላይ ለማሳረፍ ከሚረዳን እና ሁላችንን የሚያግባባን ይቅርታ፣ ሠላም፣ ፍቅር ነው፡፡
እኛ ኢትዮጵያኖች ላለፋት አመታት በብዙ አለመግባባት ውስጥ አልፈናል እያለፋንም እንገኛለን በዚህም ምክንያት ማህበራዊ ግንኙነታችን ላልቶ ይገኛል፡፡
ሆኖም ግን እንደ ሃገር ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል፡፡ እስከ መቼ በተለያየ ጥያቄና ጥላቻ ውስጥ እንጓዛለን ያለብንን ችግሮች በመቀራረብና በይቅርታ በሠላማዊ ንግግር መፍታት ይኖርብናል፡፡ ይህንን ማድረግ ካልቻልን ለልጆቻችን አላስፈላጊ የቤት ሥራ መስጠት እንዳይሆን ቆም ብለን በጋራ የሚያስተሳስሩንን ሰፊና ጥልቅ እሴቶች ያሉን እንደ መሆናችን መጠን ነጋችንን ዛሬ ላይ እንስራ እንተያይ እንቀራረብ እንወያይ፡፡
ይህንን መልካም እሳቤ በማሰብ በሲውዲን ከተለያዩ ከባለ ድርሻ አካላት ከሃይማኖት አባቶች ከተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ባደረግነው ውይይት ሰባት(7) አባላት ያሉት ጊዚያዊ ኮሚቴ ተመርጦ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ስለሆነም ጠንካራ ሃገር በጠንካራ ማህበረሰብ ትመሰረታለች ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በቀጣይ በዚህ ጉዳይ ላይ በምናደርገው ውይይት ላይ ሁላችሁም ኢትዮጵያዊያን ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን እንድትገኙልን ከወዲሁ ጥሪያችንን ማቅረብ እንወዳለን በቀጣይ ጊዜን እና ቦታውን የምናሳውቅ ይሆናል.
ጊዛዊ ኮሚቴው
Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.